በብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ሀገራዊና ተቋማዊ ዕቅድ አፈጻጸም ላይ የተቋሙ ስራ አመራር ከሠራተኞች ጋር ዉይይት አደረጉ

የብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት አመራርና ሰራተኞች የኢንስቲትዩቱን እንዲሁም የፌዴራል መንግስት ሀገራዊ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ።

የፌዴራል መንግስት ሀገራዊ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸምን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታከለ አባይነህ አቅርበዋል። በገለጻቸውም በማህበራዊ እና በኢኮኖሚያዊው እንዲሁም በተለያዩ ሴክተሮች የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ተችሏል።

ዋና ዓላማዉም ኢንስቲትዩቱ የፌደራል መንግስት ተቋም እንደመሆኑ በሀገሪቱ የሚከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠርና እንደተቋም የሚመለከተን ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት የበኩሉን አስተዋጸኦ  እንዲያደርግ ነዉ ብለዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱን የ9 ወር የኦፕሬሽናልና የፋይናንስ አፈፃፀም፣በክትባት ምርት አቅርቦት፣ በዉጭ ሃገር እና በሃገር ዉስጥ ሽያጭ፣የምርምር ስራዎች እና የተለያዩ ፕሮጀክቶች ያሉበት ደረጃ፣የገበያ መዳረሻ ከማስፋት አንጻር የተሰሩ ስራዎች እና ሌሎች ታቅደዉ የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራትን ዕቅድ አፈጻጸም እንዲሁም የታዩ ጥንካሬዎችና ተግዳሮቶችን የኢንስቲትዩቱ የፕላንና ፕሮግራም አገልግሎት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ አበራ አቅርበዋል።

የብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በሬቻ ባይሳ ባስተላለፉት መልዕክት በቀሩት ሶስት ወራት በትጋት በመስራት በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ማስመዝገብ እንደሚቻል ተናግረዋል።

በመጨረሻም በሀገራዊ እና በተለያዩ የኢንስቲትዩቱ የስራ እንቅስቃሴዎች ላይ ከሰራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በአመራሩ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በአጠቃላይ ሠራተኛውና ስራ አመራሩ በአፈፃፀም  ያጋጠሙ የዉስጥና ዉጫዊ ችግሮች ላይ ዉይይት በማድረግ ቀጣይ የኢንስቲትዩን አፈፃፀም የተሻለ ስኬት ላይ ለማድረስ ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንዳለበት አቅጣጫ ተሰጥቶ ዉይይቱ ተጠናቋል፡፡

ለዘገባዉ፡- የኢንስቲትዩቱ  ኮሙኒኬሽን

                                   ሚያዚያ 2017 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *