በብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት 8ኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተካሄደ



“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል፣ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. በብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት 8ኛው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተካሄደ። የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አመራሮችና የኢንስቲትዩቱ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር አመራሮች የተገኙ ሲሆን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ፤ ተስማሚ የሆነ አረንጓዴ አካባቢን ለመፍጠር ለምግብነት የሚዉሉ የፍራፍሬ ችግኞች፦ አቮካዶ፣ ፓፓያ፣ ሙዝ እንዲሁም ለደን ሽፋንና ለአካባቢ ጥበቃ የሚውሉ ልዩ ልዩ የችግኝ አይነቶች ተተክለዋል።
በዕለቱ የኢንስቲትዩቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ታከለ አባይነህ ባስተላለፉት መልዕክት፦ “የእንሰሳት ጤና እና የአካባቢ ጥበቃ በቀጥታ የተሳሰሩ ናቸው። ጤናማ ስነ-ምህዳር መፍጠር የምንችለው እንደዚህ ባሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሮች ላይ በንቃት ስንሳተፍ ብቻ ነው፤ የተከልናቸውንም ችግኞች ተንክባክበን የማጽደቅ ኃላፊነት አለብን” ብለዋል። የ8ኛውን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ልዩ የሚያደርገው ለችግኝ ተከላው የሚሆኑ ቦታዎች በጥናት ላይ ተመስርተው የተለዩና የዝግጅት ሥራው ቀድሞ የተከናወነ ከመሆኑም ባሻገር የተተከሉት አብዛኛዎቹ ችግኞች ለምግብነት የሚውሉ መሆናቸው ነው፡፡
ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የእንስሳት በሽታ መከላከያ ክትባት እንዲሁም መድሃኒት በማምረት የእንሰሳትን ጤና በመጠበቅ ረገድ ከሚጫወተው ሚና በተጨማሪ በተፈጥሮ ጥበቃ ላይም በንቃት ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል።



