በብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት በደንበኞች ቀን የክልል ባለድርሻ አካላት ዉይይት አደረጉ

ክልሎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት አፈጻጸማቸዉንና በቀጣይ 2015 በጀት አመት የሚያስፈልጋቸዉን የክትባት መጠንና ያጋጠሟቸዉ ችግሮች ላይ በደንበኞች ቀን መድረክ ዉይይት ተደረገ፡፡

በዉይይቱ የኢንስቲትዩቱ የቦርድ ሰብሳቢ ተወካይ፣የፌደራል የግብርና ሚኒስቴር ተወካዮች እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ እና የክልል የእንሰሳት ጤና አገልግሎት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በ2014 በጀት አመት በተቋሙ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የቀረበ ሲሆን፤በቀጣይ የመልካም አመራረት ሂደት የሚያሟላ አዲስ የዶሮ ክትባት ማምረቻ ላብራቶሪ ግንባታ እና የክትባት አመራረት ዘዴን በተሻለ ለማዘመን እንደሚሰራ የኢንስቲትዩቱን ዋና ዳይሬክተር ወክለዉ ዶ/ር በላይነህ ጌታቸዉ ገልጸዋል፡፡

በበጀት አመቱ ለክልሎች ከተያዘዉ ጠቅላላ ዕቅድ 352.4 ሚሊዮን ዶዝ ክትባት ሽያጭ የተከናወነዉ 257.9 ሚሊዮን ዶዝ ሲሆን ይህም የዕቅዱን 73 በመቶ እንደሚሸፍን የኢንስቲትዩቱ የግብይትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  አቶ መስፍን ታደሰ ገልጸዋል

የኢንስቲትዩቱ የቦርድ አባል አቶ ታደሰ ጉታ ክልሎችም ሆኑ ሌሎች ደንበኞች ከኢንስቲትዩቱ የሚወስዱትን ክትባት አገልግሎት ላይ እስከሚዉልበት ጊዜ ድረስ በአግባቡ ሊይዙ እንደሚገባ አሳስበዉ፤ ከባለድርሻ አካላት በተነሱ ጥያቄዎች  ላይ ዉይይት ተደርጎ የእለቱ መርሃግብር ተጠናቋል፡፡

የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን

መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም