ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት በታማኝ ግብር ከፋይነት የሀገር ዓቀፍ የብር/ Silver ደረጃ ተሸላሚ ሆነ




ከ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለግብር ከፋዮች የዕዉቅና እና ሽልማት ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን ፤ በ2017 በጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ታማኝ ግብር ከፋዮች በ7ኛዉ ዙር ሀገር አቀፍ የዕዉቅና እና የሽልማት ሥነ- ሥርዓት የኢፌድሪ ጠ/ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ በ7ኛው ዙር ሀገራዊ ዕዉቅና እና ሽልማት ፕሮግራም ላይ 22 የመንግስት የልማት ድርጅቶች በተለያየ ደረጃ (የፕላቲኒየም/platinum፣ የወርቅ/Gold እና የብር/ Silver) ዋንጫ ተሸላሚ ሲሆኑ ከነዚህም መካከል ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የብር/ Silver ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ የብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታከለ አባይነህ በገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን ለምስጋና በተዘጋጀዉ ፕሮግራም ላይ ተገኝተዉ ሽልማቱን የተቀበሉ ሲሆን ከሰባቱ ዙር የምስጋና ፕሮግራም ኢንስቲትዩቱ ሲሸለም የመጀመሪያዉ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱን ለዚህ እውቅና ያበቃው የተቋሙ ስራ አመረር ቦርድ፣ ማናጅመንትና የመላው ሰራተኞች የተቀናጀ ድምር ውጤት በመሆኑ፣ ዋና ዳይሬክተሩ የላቀ ምስጋናቸውን በማቅረብ፣ ኢንስቲትዩቱ የሀገር ኢኮኖሚ እድገትና ልማት አጋርነቱን ለማስቀጠል ተግቶ እንደሚሰራ አሳውቀዋል፡፡
ከእንስሳት ጤንነት እስከ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት!!!
መስከረም/2018
