የሚንስትሮች ምክር ቤት 27ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የኢንስቲትዩቱን የተፈቀደ ካፒታል አፀደቀ

የሚንስትሮች ምክር ቤት 27 መደበኛ ስብሰባ ላይ የኢንስቲትዩቱን የተፈቀደ ካፒታል አፀደቀ

የሚንስትሮች ምክር ቤት የብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት በልማት ድርጅትነት ለማቋቋም  የወጣው ደንብ ላይ  ኢንስቲትዩቱ የእንሰሳት በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስፈልጉ ክትባቶችና መድሃኒቶች፣ በእንሰሳት ጤና ረገድ ለሚደረግ  ምርምር  የሚያገለግሉ ባዮሎጂካሎችና ሪኤጀንቶችን እንዲሁም ተዛማች ግብአቶችን በራስ አቅም ለማምረት የተያዘውን አገራዊ ስትራቴጂ ማሳካት እንዲችል የኢንስቲትዩቱን ካፒታል  ማሳደጊያ ረቂቅ ደንብ ቀርቧል:: ምክር ቤቱም የኢንስቲትዩቱን የተፈቀደ  ካፒታል ብር 2.6 ቢሊዮን እንዲሆን ደንቡም በነጋሪት ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል በሙሉ  ድምፅ ወስኗል ::

የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን

                   የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *