ለሁሉም ሚዲያ ኢንስቲትዩታችን 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ  ለሚሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚዲያ ሽፋን እንዲደረግልን ስለመጠየቅ፤

 

ኢንስቲትዩታችን 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ  ለሚሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚዲያ ሽፋን እንዲደረግልን ስለመጠየቅ፤

ብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የሀገሪቱን የእንሰሳት ሃብት ከተለያዩ የእንሰሳት በሽታዎች ለመከላከል የሚያስችል ክትባቶችና መድሃኒቶችን በማቀነባበር ለተጠቃሚዎቹ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያሰራጭ የመንግስት የልማት ድርጅት ነዉ፡፡

ኢንስቲትዩቱ የእንሰሳት በሽታ መከላከያ ክትባት የማምረት ስራዉን ከ1956 ዓ.ም የጀመረ ሲሆን  ከተመሰረተ 60 አመታትን አስቆጥሯል፡፡ በዚህ የረጅም ጊዜ ጉዞዉ በምርት ብዛት ጥራትና የማምረት አቅሙን በማሳደግ አህጉራዊና ሀገራዊ ተወዳዳሪነቱን እያሳደገ ከመምጣቱም በላይ በተለይም ሀገሪቷ ከጤናማ የእንስሳት ሀብቷ የምታገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ጠንክሮ እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡

ኢንስቲትዩቱ የክትባት ምርቶቹን ለሀገር ውስጥና ከ26 ያላነሱ የአፍሪካ ሀገራት ኤክስፖርት በማድረግ የሀገራችንን የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ በመደገፍ እየሰራ ነዉ፡፡

ኢንስቲትዩቱ በዚህ በጀት ዓመት የ60ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ የምስረታ በዓሉን  ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከእንስሳት ጤንነት እስከ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት! በሚል መሪ ቃል በደማቅ ስነ-ስርዓት ያከብራል፡፡

በዓሉን መከበርና ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚካሄዱ ሁነቶችን በተመለከተ ኢንስቲትዩቱ ሐሙስ ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም የኢንስቲትዩቱ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፣የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር እና የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር  ስካይላይት  ሆቴል ከቀኑ በ 8፡00  ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ሆኖም በእለቱ የሚዲያ ተቋማችሁ ይህንን ሀገራዊ ፋይዳዉ ከፍተኛ የሆነ ታሪካዊ ሁነት ቅድመ ዝግጅት የሚዲያ ሽፋን እንድትሰጡልን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *